አርማሽ (ቀና በል) አዝማች: አርማሽ ይውለብለብ ከደጄ ልቤ ናፍቆሻል ወዳጄ እኔስ እስካይሽ ጨነቀኝ ሀገሬ መምጫሽ ናፈቀኝ ቀን እየሄደ ቀን መጣ ልቤ ከሀሳብ ሳይወጣ መጥታ ታብሰው እንባዬን ሀገሬን ጥሯት አርማዬን መቼም ከዚህ ምድር ላይ ሄዶ ነው ሁሉም ቀሪ አገር ናት ቋሚ ሰንደቅ ለዘላለም ኗሪ ትላንትም እንደ ጀምበር እያዩት ካይን ይርቃል ኢትዮጵያ እንድትመጪ ስንት ቀን ይበቃል እኔማ ላይሽ በቶሎ ምኞት ነበረኝ ግን ባባሁ ናፈኩሽ እና ዕምባ ቀደመኝ እኔማ አለሁ እስካሁን ተስፋ ሰንቄ በወንዜ ባገሬ እያለሁ አገር ናፍቄ ወጥተሽ በምሥራቅ አንቺ ያለም ጀምበር አንድ አርጊንና ጠላትሽ ይፈር የቦረኩበት በልጅነቴ የያኔው መልክሽ ብቅ ሲል ፊቴ እየመለሰኝ ወደ ትላንቱ ናፍቆኝ በብርቱ ትዝ አለኝ የጥንቱ እ … Continue reading አርማሽ ይውለብለብ !
Copy and paste this URL into your WordPress site to embed
Copy and paste this code into your site to embed